የትግሬ-ነፃ አውጭ ግንባር (ወያኔ) የዐማራውን ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ ላለፉት 42 ዓመታት የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል የፈጸመበትና አሁንም እየፈጸመበት እንዳለ በግልጽ ይታወቃል። በመሆኑም በነዚህ ዓመታት ከአምስት ሚሊዮን በላይ ዐማሮችን ከምድረ-ገጽ እንዳጠፋ የተለያዩ መረጃዎች ያስረዳሉ። በርካታ ቁጥር ያለው በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ ፣ በምሥራቅና በመሀል አገር ይኖሩ የነበሩትን ዐማሮች፣ ሀብት ንበረታቸውን ነጥቆ በማፈናቀል ለከፍተኛ ችግር የዳረጋቸው እንደሆነ ዓለም በዝምታ እየተመለከተው ያለ የዘመናችን፣ በሰዎች ላይ የተፈጸመ አሳዛኝና ዘግናኝ ወንጀል እንደሆነ በአሰቦት፣ በበደኖ፣ በአርባ ጉጉ፣ በወተር፣ በመቻሬ፣ በጉራ ፈርዳ፣ በምሥራቅ ወለጋ፣ በመተከል፣ በቤንቺ ማጅ፣ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት ፣በራያና ቆቦ ወዘተ የተፈጸሙት የዐማራ ዕልቂቶች አፍ አውጥተው እየተናገሩ ነው።
MWAO Press Releases
ዛሬ በኢትዮጵያ ምድር ዘረኛው የትግሬ ወያኔ አገዛዝ በሕዝባችን ላይ፣ በተለይም በዐማራው ነገድ ላይ የሚፈጽመው የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በ«አርበኞች ግንቦት 7» እያመካኘ ነው። ለዚህም ምክንያት የሆነው አርበኞች ግንቦት ሰባት፣ በሚቆጣጠረው የብዙኃን መገናኛ ያላደረገውን አደረኩ፣ ያላዘመተውን ወታደር አዘመትኩ፣ «የክተት አዋጁ ፊሽካ ተነፋ»፣ በሁሉም ሕዝባዊ እንቢተኝነት እንቅስቃሴዎች እኔ አለሁበት፣ የምመራው እኔ ነኝ፣ የሚለው ወሬ ቀድሞ መነዛቱ ነው። ወሬው በትንሽ ተግባር ቢደገፍ ኖሮ ባልከፋ። ክፋቱ ምንም ዓይነት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሳይጀምር፣ ኤርትራ በረሃ ከትሟል የሚባለው ፋኖ፣ የተከዜን ወንዝ ሳይሻገር፣ የወያኔ አገዛዝ አንገሽግሾት ባመቸውና በመሰለው መንገድ ጥይት የተኮሰውን ሁሉ የእኔ ነው ማለቱ፣ «ለወያኔ ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ፣ ጂግራ ናት ይሏታል» እንዲል ሠፊ በር ከፍቶለታል። በመሆኑም በርካታ ዐማሮች በአርበኞች ግንቦት 7 ስም ለሞት፣ ለእስር፣ ለእንግልትና ለስደት እንዲጋለጡ ምክንያት እየሆነ መምጣቱና ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ በመሄዱ፣ የዐማራው ነገድ ‘ አርበኞች ግንቦት 7 ለማንነታችን መከታ ያልሆነ ድርጅት፣ ለጥቃታችን ምክንያት ባይሆን ምናለበት ?’ የሚል ጥያቄ እንዲያነሳ ግድ ብሎታል።
ለ ውድ አባላት ደጋፊዎች ና የሚዲያ አውታሮች ፤
በሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ስም መጪው የፈረንጆች አመት አዲስ የሚሆንበት ድልና ነፃነት የሚገኝበት ይሆንልን ዘንድ ልባዊ ምኞታችንን ለመግለጽ እንወዳለን።
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
ድንገተኛ ጎርፍ አምጥቷቸው የጀግንነት ከበሮ ሲደልቁ የቆዩት ወያኔዎች እራሳቸው ተደልቀው የታሪክ ትቢያ የመሆናቸው ጊዜ ብዙ ያዘግማል የሚል ግምት የለም። እነዚህ ጎጠኞች የዘሩት የጎጥ ዘር እራሱ ሊጠራርጋቸው አፉን ከፍቷል። ወትሮውንም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ብሄረሰቦች ባሉበት አገር እንኳን እንደወያኔ ያለው የለየለት ዘረኛ ጉጅሌ ይቅርና አናሳዎች ፤ስልጣን ላይ ሲወጡ እምነት በማጣት ሌሊት ተቀን ሲባንኑ ፣ሲገድሉ ፣ ንጹሃንን ወደ ወህኒ ማጋዝ ስራቸው እንደሆነ ይታወቃል።
በአሁኑ ዘመን በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉ ነገር እያለው ሁሉንም ያጣ ዜጋ ዐማራው ነው ቢባል የተጋነነ ነው ሊባል አይችልም። በግልጽ እንደሚታወቀው፣ ዐማራው ቋንቋው አማርኛ ነው። ይህንን ቋንቋውን ከሌሎች የኢትዮጵያ ጎሣዎች ቋንቋዎች ጋር አጣጥሞ በማሳደግ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ መግባቢያ እንዲሆን አበርክቷል። ይሁን እንጂ፣ በአሁኑ ጊዜ የአማርኛ ቋንቋ ለዐማራው ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ተለይቶ መከበሪያው መሆኑ ቀርቶ መጠቂያው ሆኗል። በአማርኛ ቋንቋ የሚጻፉት፣ በሬድዮ እና በቴሌቪዥን የሚቀርቡት ዝግጅቶች በአብዛኛው ማለት ይቻላል፣ ዐማራው የሚወገዝባቸው፣ የሚዋረድባቸው እና የሚኮነንባቸው እየሆኑ ከመጡ ዓመታትን ተሻግረው ዘመናት ተቆጥረዋል። ስለሆነም ዐማራን እና አማርኛን በጠላትነት ፈርጀው የጥፋት ተግባራቸውን ለፈጸሙና ለሚፈጽሙ ኃይሎች አጸፋውን በመስጠት፣ የአማርኛ ቋንቋም ሆነ የዐማራ ነገድ ተገቢ ቦታቸውን እንደያዙ እንዲቀጥሉ ለማስቻል፣ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ተመሥርቶ ሠፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል። ከሞረሽ ወገኔ የተግባር እንቅስቃሴዎች ውስጥ የዐማራው ድምፅ የሆነ፣ የዐማራ ድምፅ ሬድዮን ማቋቋሙ አንዱ ነው።
ምንም ጊዜው ቢረዝም፣ የመከራ ጊዜ አይረሳም። ያለፉት 25 ዓመታት የትግሬ ወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈጸመው ሁለንተናዊ በደል ምንጊዜም የሚረሳ አይደለም። እንርሳህ ብንለው ሊረሳ የሚቻል አይደለምና! ላለመረሳቱ ምክንያት የሚሆነውም እያንዳንዱ በደል በድምፅ፣ በምስል፣ በሰነድ ተመዝግቦ የተያዘ ከመሆኑም ባሻገር፣ የበደሎቹ ዓይነት በዓለም ላይ ያልታዩ ዘግናኝና ሰቅጣጭ በመሆናቸው፣ እንርሳው ብንል ከኅሊናችን ጓዳ ተሽጠው የሚረሱ አይሆኑም። «ሥራ ለሠሪው፣ እሾህ ላጣሪው» እንዲሉ፣ 25 ዓመታት ዐማራውን በአውራ ጠላትነት ፈርጆ፣ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል የፈጸሙበት የትግሬ ነፃ አውጭ ነፍሰ በላ፣ ወመኔዎች፣ እንደአንበሣ በአገሱበት አደባባይ፣ እንደውሻ ጅራታቸውን ቆልፈው እግሬ አውጭኝ ለማለት የኢምባሲዎችን በራፍ በማንኳኳት ላይ እንደሚገኙ መረጃዎች እያመለከቱ ነው። አዲስ አበባ ሱቆች ተዘግተዋል። የመንግሥት ቢሮካራሲ ተበጣጥሷል። ለዓመታት በግፍ የታሰሩ እስረኞች በሕዝባዊ እንቢተኝነቱ እንቅስቃሴ ከእስር ተለቀዋል። ባለሥላጣኖች እንዳይሸሹ የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ በጥብቅ እየተጠበቀ ነው።
የተከበራችሁ እህት ወንድሞቼ የእናት ኢትዮጵያ ልጆች! ለወገናችን ድምፅ ለመሆን ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የመጣችሁ ውድ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያዊያት! ይህ የዛሬው የተቃውሞ ሰልፍ፣ የትግሬ ነፃ አውጭ ድርጅትን ዘረኛ አገዛዝ በመቃወም ብቻ የሚገልጽ ሳይሆን፣ የወያኔ ቡድን በልኩ ቀልሶ ካስገባን የጎሣ ጎጆዎች መውጣታችንና ወያኔ የቀማንን ኢትዮጵያዊ ማንነታችንና አንድነታችን መልሰን የተጎናጸፍን መሆንችን ለዓለም ማኅበረሰብ ያሳየንበት ሕዝባዊ ሰልፍ ነው። ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ «ነብር ዝንጉርጉርነቱን፣ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን» የሚለውጠው የለም ሲል የተገለጸው ቃል ኅያው መሆኑን ማሳያ ነው።
ዐማራው ከ1972 እስከ 2008 ዓም ባሉት ዓመታት በዘረኛው የትግሬ ወያኔ በጠላትነት ተፈርጆ ከፍተኛ የሆነ የዘር ጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል የተፈጸመበት መሆኑን ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ባለፉት አራት ዓመታት ተከታታይ መግለጫዎችን ማውጣቱ ይታወሳል። በዚህም መሠረት በአጠቃላይ በወያኔ የዘር አገዛዝ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዐማሮች ከምድረ-ገጽ እንዲጠፉ ተደርጓል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ፣ ከዐማራው የጸዱ አካባቢዎችን ለመፍጠርና ዐማራውን አሰቃይቶ፣ አደህይቶና ከሰው በታች አድርጎ ተዋራጅ ለማድረግ ሀብት ንበረታቸውን በመንጠቅ ተባረዋል። አያሌዎች ለእስርና ለእንግልት ተዳርገዋል። በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እንዲሰደዱ ተደርጓል።
የተከበርከውና ጀግናው የዐማራ ሕዝብ ሆይ!
የትግሬ ወያኔ አገዛዝ «ዐማራውን አከርካሪውን ሰብረነዋል»፣ «ዐማራው ላይመለስ ገድለን ቀብረነዋል» በማለት ይሳለቅብሃል። በእርግጥም ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ከአምስት ሚሊዮን በላይ ዐማሮችን ገድሎ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ደግሞ አሰድዶ ከመኖሪያ ቀያቸው አፈናቅሏል። ሆኖም ግን ከሞቱት በላይ፣ ካሉት በታች ሆነህ የምትኖረው የቀረኸው ዐማራ፣ ከገባህበት የቁም መቃብር ለመውጣት ዘወትር ትግልህን እንዳላቋረጥክ እኛ አብረንህ የምንታገለው ልጆችህ ቀዳሚ ምሥክሮችህ ነን። በተለይም ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ መግነዝህን ቀደህ እና በጣጥሰህ፣ የተጫነብህን የመቃብር ድንጋይ እና አፈር ፈነቃቅለህ ከፈጽሞ ጥፋት ራስክን ለማዳን እያደረግኸው ላለው ተጋድሎ እና የጀግንነት ተግባር ያለን አድናቆት እና አክብሮት እጅግ ከፍ ያለ ነው። ለምታደርገው ራስክን ከፈጽሞ ጥፋት የመታደግ ተፈጥሮአዊ የመከላከል ትግል፣ እኛ በስደት የምገኝ ልጆችህ ምንጊዜም ከጎንህ የማንለይ መሆኑን ስናረጋግጥልህ በታላቅ አክብሮት እና ወገናዊነት ነው።