MWAO Press Releases

Thursday, August 25, 2016

ወያኔ አጥፍቶ ለመጥፋት የመጨረሻውን መሰናዶ እያደረገ መሆኑ ግልፅ ሆኗል

የትግሬ-ወያኔ ላለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ፣ በተለይም በዐማራው፣ በኦሮሞው፣ በሱማሌው፣ በሐዲያው፣ በአኙዋኩ፣ በኑዌሩ፣ በከፊቾው፣ ወዘተርፈ ላይ የፈጸመው የዘር ፍጅት፣ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ሊፈጸም ቀርቶ ለማሰብ አስቸጋሪ ነው። ግፉ ከገደቡ አልፎ በመትረፍረፉ፣ የዚህ የከፋ የዘር ፍጅት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ሰለባ የሆኑት ነገዶች ተወላጆች፣ በዳያቸው የሆነውን የትግሬ-ወያኔ በቃህ ካሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። ለዚህ ማረጋገጫውም፣ በየአካባቢው በባዶ እጃቸው እስከ አፍንጫው ከታጠቀው ገዳይ ኃይል ፊት በመቆም በተከታታይ የሚያሰሙት የተቃውሞ ድምፅና ሰላማዊ ሰልፍ በግልጽ ያሳያል።

የትግሬ-ወያኔ ትውልድ በምድጃ ዙሪያ ከአያት ቅድመ-አያቶቹ ተግቶት ያደገው የዐማራ ጥላቻ እጅግ የሠፋና ሥር የሰደደ መሆኑ ይታወቃል። ለዚህም ሥር የሰደደ ጥላቻ ዋና ማሳያው፣ ገና የትጥቅ ትግል ሲጀምር፣«የትግራይ ሕዝብ ደመኛ ጠላት ዐማራ ነው!»፣ «ወያኔ ዐማራን ሳያጠፋ አንዳችም እረፍት አይኖረውም!» የሚል »መሪ ሀሳብ» በፕሮግራሙ ነድፎ መንቀሳቀስ የጀመረ መሆኑ ነው። በዚህ ጥላቻ ላይም ተመሥርቶ፣ ዘረኛው አገዛዝ ባለፉት 25 ዓመታት ብቻ  ከ5 ሚሊዮን በላይ ዐማሮችን ከምድረ-ገጽ አጥፍቷል። ሌሎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ዐማሮች ለዘመናት ከኖሩበት አካባቢ ሀብት ንብረታቸውን ነጥቆ በማባረር ለከፍተኛ ችግር ዳርጓቸዋል፤ በቁጥር ከአንድ ሚሊዮን ተኩል የማያንሱትን ዐማሮች ከኢትዮጵያ ምድር አሰድዷል። ይህ በዐማራ ጥላቻ ተወልዶ ያደገና ዐማራን ለማጥፋት የተደራጀ ዘረኛ ቡድን፣ ካለፈው ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ፍትኅ በጠየቁ የዐማራው ተወላጆች ላይ የዘር ፍጅት በመፈጸም ላይ መሆኑን የዓለም የመገናኛ ብዙኃን በሥፋት እየዘገቡት መሆኑ ይታወቃል።

Wednesday, August 24, 2016

የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ አባሎቹና ደጋፊዎቹ እንዲሁም ሞረሽ የዐማራ ሬድዮ ድምፅ ፕሮጀክትን የሚደግፉ ኢትዮጵያን ክሆኑ ወገኖቻችን ጋር በቴሌኮንፈረንስ(በሥልክ) ስብሰባ ለማድረግ አቅዷል። ስብሰባው ቅዳሜ  ቀን  ነሓሴ ፳፩ ፤፪ሺህ ፰ዓ.ም(August 27፣2016) በኒዮርክ ሰዓት አቆጣጠር በ3:00PM ይጀመራል። የስብሰባው ዓላማ ሞረሽ የዐማራ ሬድዮ ድምፅ ፕሮጀክትን እውን ለማደረግ የሚያስችል የገንዘብ እና ሌሎች ዓይነት ድጋፎችን ለማሰባሰብ ይሆናል። ስለሆነም የዐማራ ጉዳይ የኢትዮጵያ ጉዳይ ነው የምትሉ ሁሉ በዕለቱ የስብሰባው ተካፋይ እንድትሆኑ በአክብሮት ተጋብዛችኋል። ስብሰባውን ለመካፈል እንደምትኖሩበት አገር በመጀመሪያ የስልክ ቁጥሩን በመደወል እና ከዚያም የመግቢያ ቁልፍ በመጠቀም መሣተፍ ይቻላል ።  

Thursday, August 18, 2016

ዘረኛው የትግሬ ወያኔ የወልቃይት ጠገዴን የማንነት ጥያቄ ደግፈው በወጡ የባሕርዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ በግፍ የገደላቸው ወገኖቻችን ዝርዝር በከፊል።

«የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ፣ የእኛም የዐማራነት ጥያቄ ነው፣» ብለው እሑድ ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓም ላይ በባሕርዳር ከተማ፣ በሰላማዊ መንገድ ድምፃቸውን ለማሰማት በወጡ ዐማሮች ላይ፣ የትግሬ ወያኔ ዘረኛ ቡድን በርካታ፣ ሩቅ አሳቢ፣ ለሥራ የጓጉ፣ ላገርና ለወገን ታላቅ ተስፋ ሰንቅው የነበሩ የአያሌ ወጣቶችን ሕይዎት በግፍ ነጥቋል። በባሕርዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ ወያኔ ከገደላቸው በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች መካከል ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን የከፊሎቹን አገኝቷል።

ከሰንጠረዡ ለመረዳት እንደሚቻለው፣ በግፍ ከተገደሉትና ዝርዝራቸውን ማወቅ ከተቻለው አርባ ዘጠኝ(49) ሰዎች ውስጥ፣ ዕድሜአቸው ሰላሳና ከዚያም በላይ የሆኑት ስምንት ( 8) ብቻ ነው። አርባ አንዱ (41) በወያኔ የግፍ አገዛዝ የተወለዱና ወያኔ ሲገባ ከአምስት ዓመት ዕድሜ የማይበልጡ መሆኑ በግልጽ ይታያል።  በመሆኑም  ያለፈውን ሥርዓት የማያውቁ፣ ያልኖሩበት፣ በትህምርትም ያልተማሩት በመሆኑ የሚናፍቁት አንዳች ነገር ይኖራ ተብሎ አይታሰብም።  ወጣቶቹ ሰዎች ናቸው እና እንደማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር መልካም ነገርን፣ እንደሰው ዕኩል መታየትን፣ ጥሩና መልክ ነገሮችን የመመኘት፣ ራሳቸውን ከሌሎች አቻዎቻቸው ጋር አመዛዝኖ ለእኛ ለምን ሰብአዊ መብቶቻችን፣ ተዘዋውሮ የመሥራትና ያመኑበትን በግልጽ የመናገር፣ የመደራጀት፣ ወዘት መብትና ነፃነት እንነጠቃለን፣ ከዚህ ሁሉ በላይ ማንነታቸውን ለምን ይካዳል ብለው መጠየቃቸው ሰው ሆኖ በመፈጠራቸው ብቻ የተሰጣቸው መብት እንጂ፣ ያለፈ ሥርዓት የመናፈቅ ወይም ትምክህተኛ የመሆን ውጤት አይደለም።

Wednesday, August 17, 2016

የትግሬ ወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ላይ ላለፉት 25 ዓመታት ጭኖት የኖረው በዘረኝነት ላይ የተመሠረተው ያንድ ነገድ የበላይነትና የውስጥ ቅኝ አገዛዝ ሥርዓት በሕዝቡ የእንቢተኝነት እንቅስቃሴ ከመኖር ወደ አለመኖር እየተሸጋገረ ነው። የወያኔ አገዛዝ ሲጀመር ጀምሮ ደካማ «መንግሥት» እንደሆነ ይታወቃል። የድክመቱ መገለጫም፣ አንደኛ፣ የአናሳዎች መንግሥት በመሆኑ የአብዛኛውን ሕዝብ ድጋፍ ያገኘ አይደለም። ሁለተኛ፣ የሚገዛው በኃይል በጦር መሣሪያ አስገድዶ እንጂ፣ በሕግ የበላይነት ተወዶና ተፈቅሮ አይደለም። ምንጊዜም በኃይል ሕዝባቸውን የሚገዙ አገዛዞች ደካማዎች እንደሆኑ የፖለቲካ ሣይንስ ሀሁ ይነግረናል። ወያኔም ከአፈጣጠሩ፣ከሚያራምደው የዘር ፖለቲካና ከባሕሪው በሚመነጭ ምክንያት ደካማ ነው። ሦስተኛው ወያኔ ከድክመቱ ብዛት የተነሳ፣ ራሱ እመራበታለሁ ብሎ፣ «በሕዝብ ተሳትፎ አጸደቁት ላለው ሕገ መንግሥት» ተገዥ አለመሆኑ የድክመቱ ሁሉ መገለጫ ነው። ይህም በመሆኑ፣ ሲጀምር ጀምሮ የወያኔ አገዛዝ፣ ደካማ ነው። ደካማ መንግሥት ደግሞ መውደቁ የግድና አይቀሬ ነው።

Tuesday, August 16, 2016

ላለፉት 25 ዓመታት የትግሬ-ወያኔ በሕዝብ ላይ የፈጸመው ግፍና በደል ከመጠን በላይ በመሆኑ፣ ሕዝቡን ለእምቢተኝነት አነሳስቷል። ይህ ግፍና በደል መጠን የለሽ በመሆኑ፣ በአገሪቱ ልዩ ልዩ ክፍሎች፣ በተለይም በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋ፣ በወሎ፣ በሐረርጌ፣ በአርሲና በወለጋ ክፍለ-ሀገሮች የሚኖረው ሕዝብ፣ የትግሬ-ወያኔ «ለብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ዕኩልነት» ሲል «አመጣሁት» ያለውን «ሕገ-መንግሥት» የማይቀበለው መሆኑንና፣ የዚሁ  «ሕገ-መንግሥት» ተብየ መገለጫ የሆነውን ሠንደቅ ከተሰቀለበት በማውረድ፣ ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መገለጫ፣ የነፃነት ቀንዲል የሆነችው ሠንደቅ ከፍ-ብላ እንድትውለበልብ እያደረገ መሆኑ በግልጽ ተስተውሏል። ይህም የትግሬ-ወያኔ አመጣሁት ያለው ዕኩልነትና የነገዶች አንድነት ውሸት መሆኑን፣ ባንፃሩ ግን የትግሬ-ወያኔ የውስጥ ቅኝ ገዥ ኃይል እንደሆነ፣ በተከታታይ በተደረጉት የሕዝባዊ እንቢተኝነት ሰላማዊ ሰልፎች በግልጽ ታይቷል።

Saturday, August 13, 2016

ኢትዮጵያ ሕዝብ በትግሬ ወያኔ ቅኝ ተገዥ ከሆነ ድፍን 25 ዓመት ሆነው። በእነዚህ ረጅም ዓመታት፣ የተማሩትም ሆነ ያልተማሩት ዜጎች፣ በቅኝ ተገዥነት መያዛቸውን ያወቁትም ሆነ ለማወቅ የጣሩት በጣም ጥቂቶች ናቸው። እነዚህ በቅኝ ተገዥነት ተይዘናል ያሉት የጥቂቶቹ ድምፅ፣ በብዙኃኑ፣ ከሁሉም በላይ በጎሣ ፖለቲከኞቹ ድምፅ ተውጦ፣ ወያኔ፣ ያላንዳች ሀግ ባይ፣ ሩብ ምዕተ ዓመታት  የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅምና ሉዓላዊነት በእጅጉ የጎዱ ሥራዎችን እንዲሠራ ሠፊ ዕድል ሰጠው። በመሆኑም የኢትዮጵያዊነት አያያዥ ማገርና ወራጅ፣ መሠረትና ጭምጭም የነበሩትን፣ የኢትዮጵያዊነት ዕሴቶቻችን ከሥራቸው ነቀላቸው። ሕዝቡን በነገድ ከፋፍሎ እሣትና ጭድ አደረጋቸው። የኢትዮጵያ ነገዶች ሙጫ በመሆን ከሌሎች ነገዶችና ጎሣዎች ጋር ሰምና ፈትል ሆኖ፣ ኢትዮጵያዊነትን ሲገነባ የኖረውን የዐማራ ነገድ፣ በዘር ጠላትነት ፈርጆ፣ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ፈጸመበት። አምስት ሚሊዮን ዐማራ ከምድረ ኢትዮጵያ እንዲጠፋ ተደረገ። በወለጋ፣ በኢሉባቡር፣ በከፋ፣ በሐረርጌ፣ በጎጃምና በጎንደር ይኖሩ የነበሩትን ዐማሮች በግፍ ሀብት ንብረታቸውን ነጥቀው ለርሃብ፣ ለድህነትና ለአገር አልባነት አሳልፎ ሰጣቸው። ይህ ዓለም በዝምታ እየተመለከተው ያለው የዘር ጥቃት፣ ዛሬ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት ዐማሮች የቅኝ አገዛዙን ሰንሰለት በጣጥሰው፣ ፍፁም ነፃ የሆነ ዐማራዊ ማንነታቸውን አረጋግጠው፣ የኢትዮጵያን ትንሣዔ ለማብሰር ከአፋኙ የወያኔ የስለላና የአፈና መዋቅር ኃይል ጋር የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ይገኛሉ።

የዐማራው ነገድ ዛሬ በትግሬ ወያኔ ቅኝ ተገዥ መሆኑን ከማወቅ አልፎ፣ ለነፃነቱ ቆርጦ የሕይዎት መስዋዕትነት እየከፈለ ነው። በዚህ የሞት ሽረት ትግል ውስጥ፣ እስካሁን በጎንደር ከተማ፣ አዘዞ፣ ቆላድባ፣ አርማጭሆ፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ወልቃይት፣ ጋይንት፣ ደብረታቦር፣ ባሕር ዳር ወዘተርፈ ቁጥራቸው ገና በውል ያላወቅናቸው አያሌ ወንድምና እህቶቻችን ባልሞ ተኳሾች የጥይት አረር ወድቀዋል። በርካቶቹ በወያኔ እስር ቤቶች የመከራን ጽዋ እየተቀበሉ ነው። ዐማራውን ለዚህ ግፍ ያበቁት በወያኔ የመከላከያ፣ የፖሊስና የፀጥታ ሠራቶች የተቀጠሩ ብቻ ሳይሆኑ፣ ከሕዝቡ ጋር የሚኖሩት በየኮንዶሚኒየሙ በሰፈራነት የተሰገሰጉት ትግሬዎች መሆናቸውን ስንገነዘብ፣ «ለካ እስከ ዛሬ በጉርብትናም ሆነ በጋብቻ ከእነዚህ ሰዎች ጋር የፈጠርነው ግንኙነት፣ እኛን ለማጥቂያ ውስጣችንን ገልጠው እንዲያዩን ሁኔታዎችን ያመቻቸ ነው፤» ብለን እንድናስብ አስገድደውናል።

Sunday, August 7, 2016

ዐማራው የኢትዮጵያዊነት ዋልታና ማገር፣ ወራጅና ጭምጭም፣ ስሚንቶና አሸዋ መሆኑ ይታወቃል። ይህን ማንነቱን ጠንቅቀው የሚያውቁ፤ የአገርና የትውልድ ከኻዲዎች፣ ዐማራውን የሌሎች ነገድና ጎሣዎች ጠላት አድርገው በመሳል፣ ላለፉት ፳፭(ሃያ አምሥት) ዓመታት የዘረኛው የትግሬ ወያኔ አገዛዝ፣ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል እንዲፈጸምበት አድርገዋል። በመሆኑም በቁጥር ከአምስት ሚሊዮን የማያንሱ ዐማሮችን በልዩ ልዩ መንገዶች ከምድረ-ገጽ እንዲጠፉ አድርገዋል። አንዳንድ አወቅን የሚሉ፣ የማንነት ቀውስ ውስጥ የገቡ ሰዎችም «ዐማራ የሚባል ነገድ የለም» እስከ ማለት የደረሱ መኖራቸውን፣ ዐማራው በትዕግሥትና በትዝብት ሲያያቸው እንደኖረ ይታወቃል። ወያኔም በትዕቢት ተወጥሮ፣ ዐማራን «ፈሪ፣ ሽንታም፣ ወራሪ፣ ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ»፣ ወዘተርፈ እያለ የዐማራን ዘር ከመግደልና ከማንገላታት አልፎ፣ መልካም ስምና ታሪኩን ጥላሸት ሊቀባ መሞከሩ በግልጽ ይታወቃል። ሆኖም፣ ሁሉም ነገር ገደብና ወሰን አለውና፣ የዐማራው ድምፅ ከፍ ብሎ እንዲሰማ በቆራጥነት የቆሙት ልጆቹ ባሰሙት ጩኸት፣ ይኸውና የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የዐማራው ሕዝብ ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ፣ በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ፋና ወጊነት የተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመጽ ጎንደር ከተማን፣ አዘዞን እና ደንቢያን አካቶ፣ በዛሬው ዕለት ማለትም ሐምሌ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ሕዝባዊ አመጹና እምቢተኝነቱ ወደ ገብርየ አገር፣ «ራስ ጋይንት» ተሸጋግሮ ውሏል። የራስ ጋይንት ሕዝብ የወያኔን የስለላና የአፈና መዋቅር በጣጥሶ፣ «ወልቃይት ጠገዴ ዐማራ ነው!»፣ «ደንበራችን ተከዜ ነው!»፣ «አላማጣ፣ ሰቆጣ የዐማራ ነው!»፣ « የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች፣ ኮሎኔል ደመቀ፣ አንዱዓለም አራጌ፣ እስክንድር ነጋ ይፈቱ! በኦሮሞ ወንድሞቻችን ላይ የተከፈተው ጥቃት ይቁም!» እያሉ፣ ዐማራዊ ማንነታቸውን አስረግጠው፣ ጀግንነታቸው በኢትዮጵያነት የተለወሰ ኅብር መሆኑን አሳይተዋል። 

Thursday, July 14, 2016

የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምትና አርምጭሆ ወረዳ ነዋሪ የዐማራ ነገድ ሕዝብ ፣በዘረኛው የትግሬ ወያኔ ከ1972 ዓም እስከ ዛሬ ድረስ የማያባራ ፣አሰቃቂ፣ ሰቅጣጭና አሳዛኝ ግፍ ፈጽሞበታል። እየፈጸመበትም ይገኛል። በሽዎች የሚቆጠሩትን በአሰቃቂ ሁኔታ አሥሮና አሰቃይቶ ገድሏል። አያሌዎች ዐማራ በመሆናቸውና በኢትዮጵያ አንድነት ማመናቸው እንደወንጀል ተቆጥሮባቸው በግፍ በመሬት ውስጥ እስር ቤቶች ያለፀሐይ ብርሃን ለዘመናት ታስረው ተሰቃይተዋል። በርካታ የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ጠለምት ነዋሪ አዛውንቶች ንብረታቸውን በወያኔ ተወርሰው ለድህነት ተዳርገዋል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት በትውልድ አገራቸው ሠርቶ ለመኖር ባለመቻላቸው ለስደት ተዳርገዋል። በርካታ ልጃገረዶችና የአባወራ ሚስቶች በወያኔ አፋኝ ቡድን ተደፍረዋል። ጥንተ የወረዳዎቹ ነዋሪ የዐማራ ነገድ ተወላጆች አጽመ ርሳታቸውን ተነጥቀው ለትግሬ ሠፋሪ ተሰጥቷል።

Friday, May 6, 2016

ከዛሬ ሰማኒያ ዓመታት በፊት የነበሩት ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን እና እናቶቻችን፣ ከትግራይ እና ከኤርትራ ምድር በበቀሉ ባንዶች አጋዥነት በፋሽስት ጣሊያኖች ጦር ማይጨው ላይ ድል ሲመቱ «እሺ፣ አሜን፣ እንገዛለን» ብለው እጃቸውን አጣጥፈው አልተቀመጡም። ራሣቸው ፋሽስቶችም እንዳመኑት፥ በተለይ በሰሜን ሸዋ፣ በጎጃም፣ በጎንደር፣ በወሎ፣ በጉራጌ፣ በጅባት እና ሜጫ እንዲሁም በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የነበሩት አርበኞች በመረጧቸው የጎበዝ አለቆቻቸው እየተመሩ፣ ለአምሥት ዓመታት የፋሽስት ጣሊያንን ጦር ከእነ ባንዳ ግሣንግሱ መውጫ መግቢያ አሣጥተውታል። ከዚያም ከየካቲት 1933 ዓም ጀምረው ጀግኖች አርበኞቻችን ባደረጉት የተቀነባበረ የጥቃት ዘመቻ ልክ የዛሬ 75 ዓመት ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓም በቀዳማዊ ኃይለሥላሤ መሪነት በድል አድራጊነት ዋና ከተማችንን አዲስ አበባን ለመቆጣጠር በቅተዋል። ሆኖም ዛሬ ላይ ሆነን ስናየው ያ ሁሉ መስዋዕትነት ያስገኘልንን ብሔራዊ ክብር እና ልዕልና እንዲህ አሽቀንጥረን እንድንጥል ያደረገንን ምክንያት ለመገንዘብ ትልቅ እንቆቅልሽ ይሆንብናል። 

Saturday, April 30, 2016

ዓለምን የፈጠረ የዘላለም አምላክ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚች ዕለት ግንዛቴን ፍቱልኝ ፤ ድንጋዩንም ፈንቅሉልኝ ሳይል በባሕርይ ኃይሉና ስልጣኑ ተነስቷል። በእርግጥም አምላካችን በሞቱ ሞትን ገድሎ በትንሣኤው ሕይወትን ችሮናልና ደስታ ይገባናል። አምላካችን ወልድ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሣኤው በረከትና የውስጥ ነፃነት አይለየን። በዚች ቅዱስ ቀን ሊያዝን የሚገባው እግዚአብሔር አምላክ በአምሳያው የፈጠረውንና የሚያከብረውን ሰው - ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያለምንም ጥፋትና ወንጀል በስግብግብነትና ከንቱ ጥላቻ በመታወር እንደሙጃ የሚያጭደውና የሚጨፈጭፈው የትግሬ ወያኔ ቡድን ነው። በጌታችን እና በመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የሚደነግጡትም ሆነ የሚታወኩት እነዚሁ በአጋንንት መንፈስ የሰከሩና በአራዊት ባሕርይ ያደጉት ካህዲዎች ናቸው። የተዘራው የሚታጭድበት ያች ጎደሎ ቀናቸው አይቀሬ ናትና በዕለተ ትንሣኤዋ ፊታችንን ወደፈጣሪያችን ማዞር ይጠበቅብናል። ኢትዮጵያም አጆቿን ወደ ኃያሉ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።

Pages