Amharic

ዐማራው፣ ዐማራዊ ማንነቱን አረጋግጦ፤ ጀግንነቱንና ኢትዮጵያዊነቱን በደሙ እያስከበረ ነው!

Sunday, August 7, 2016

ዐማራው የኢትዮጵያዊነት ዋልታና ማገር፣ ወራጅና ጭምጭም፣ ስሚንቶና አሸዋ መሆኑ ይታወቃል። ይህን ማንነቱን ጠንቅቀው የሚያውቁ፤ የአገርና የትውልድ ከኻዲዎች፣ ዐማራውን የሌሎች ነገድና ጎሣዎች ጠላት አድርገው በመሳል፣ ላለፉት ፳፭(ሃያ አምሥት) ዓመታት የዘረኛው የትግሬ ወያኔ አገዛዝ፣ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል እንዲፈጸምበት አድርገዋል። በመሆኑም በቁጥር ከአምስት ሚሊዮን የማያንሱ ዐማሮችን በልዩ ልዩ መንገዶች ከምድረ-ገጽ እንዲጠፉ አድርገዋል። አንዳንድ...Read more

«የማይመቱት ልጅ፣ ሲቆጡት ያለቅሳል!»

Wednesday, July 27, 2016

የጐንደሩ ጉዳይ የዐማራውን ኅልውና የማስከበሩ ትግል የመጀመሪያው ምዕራፍ እንጂ የመጨረሻው እንዳልሆነ ይታወቅ!

ሰሞኑን የሞሶሎኒ ዓላማ አራማጅ የሆነው ዘረኛው የትግሬ ወያኔ አረመኔአዊ አገዛዝ፤ ባለፉት 40 ዓመታት በወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ በተናጠል፤ በዐማራው ነገድ በጥቅል፤ የሚፈጽመው የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋርሯል። በቅርቡም ባካሄደው ዘግናኝና ሰቅጣጭ ግድያና ሥቃይ፣ እስራት...Read more

የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት የማዕከላዊ ምክርቤት 8ኛ መደበኛ ስብሰባ

Wednesday, July 27, 2016

እኛ የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማዕከላዊ ምክር ቤት አባሎች፣ በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት የማዕከላዊ ምክርቤቱን 8ኛ መደበኛ ስብሰባ ቅዳሜ ሰኔ 25 ቀን 2008 ዓ.ም. (Saturday July 2, 2016) አድርገናል። ምክር ቤቱ፦

አንደኛ፦ በሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ሊቀመንበር የቀረበውን የማዕከላዊ ምክር ቤቱን የስድስት ወር የሥራ ሪፖርት አዳምጠን በሙሉ ድምፅ አጽድቀናል።Read more

«የእሣት ልጅ አመድ» የሆነው የዘመኑ ኢትዮጵያዊ ታሪካዊ ማንነቱን ያስከብር!

Friday, May 6, 2016

ከዛሬ ሰማኒያ ዓመታት በፊት የነበሩት ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን እና እናቶቻችን፣ ከትግራይ እና ከኤርትራ ምድር በበቀሉ ባንዶች አጋዥነት በፋሽስት ጣሊያኖች ጦር ማይጨው ላይ ድል ሲመቱ «እሺ፣ አሜን፣ እንገዛለን» ብለው እጃቸውን አጣጥፈው አልተቀመጡም። ራሣቸው ፋሽስቶችም እንዳመኑት፥ በተለይ በሰሜን ሸዋ፣ በጎጃም፣ በጎንደር፣ በወሎ፣ በጉራጌ፣ በጅባት እና ሜጫ እንዲሁም በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የነበሩት አርበኞች በመረጧቸው የጎበዝ አለቆቻቸው እየተመሩ፣ ለአምሥት...Read more

ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያን በሙሉ! እንኳ ን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ።

Saturday, April 30, 2016

ዓለምን የፈጠረ የዘላለም አምላክ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚች ዕለት ግንዛቴን ፍቱልኝ ፤ ድንጋዩንም ፈንቅሉልኝ ሳይል በባሕርይ ኃይሉና ስልጣኑ ተነስቷል። በእርግጥም አምላካችን በሞቱ ሞትን ገድሎ በትንሣኤው ሕይወትን ችሮናልና ደስታ ይገባናል። አምላካችን ወልድ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሣኤው በረከትና የውስጥ ነፃነት አይለየን። በዚች ቅዱስ ቀን ሊያዝን የሚገባው እግዚአብሔር አምላክ በአምሳያው የፈጠረውንና የሚያከብረውን ሰው - ኢትዮጵያዊ ዜጋ...Read more

ከ1983 እስከ 2007 ዓ.ም በዐማራው ነገድ ተወላጆች ላይ ስለደረሰው የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል የጥናት ውጤት ማጠቃለያ ዘገባ (ክፍል 2)

Thursday, April 28, 2016

ሀ)   መግቢያ

ኢትዮጵያ ውስጥ በአንድነት ሃይሎችና በጎጠኞች መካከል የተካሄደው ፍልሚያ ፤ በጎጠኞች አሸናፊነት ከተደመደመ ወዲህ እራሱን የቻለ የፖለቲካ ውጥንቅጥ እስከትሎ እንደሚመጣ የተገመተ ቢሆንም ወደ ዘር ማጥፋትና ማጽዳት ያመራል ብሎ የተነበየ ከቶ አልነበረም። የጎጠኞች ያልተጠበቀ ድልና እሱንም ተከትሎ የመጣው ስካር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዐማሮችን ደም አፍሷል፤ እያፈሰሰም ነው። ክረምትና በጋ ፣ ቁር ፣ ሃሩር ሳይለይ ሌት...Read more

ዐማራው ከወልቃይት፣ጠገዴ እና ጠለምት ሕዝብ ጥያቄ ጎን ሊቆም ይገባዋል!

Friday, April 8, 2016

የማንኛውም አመፅ መነሻ መሠረቱ፣ ገዥዎች በሕዝብ ላይ የሚያደርሱት፣ የኢኮኖሚ ብዝበዛ፣ የመብት ረገጣ፣ የማንነት ነጠቃ እና የሥነ-ልቦና ሰለባ ልኩን አልፎ ገደብ ሲጥስ የሚፈጥረው ምሬት እንደሆነ ይታወቃል። የትግሬ ወያኔ ዘረኛ እና ከፋፋይ የፋሽስት ሞሶሎኒ ዓላማ አራማጅ ቡድን፣ በወልቃት ፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በሠቲት እና በአርማጭሆ ሕዝብ ላይ በተናጠል፣ እንዲሁም  በዐማራው ነገድ ላይ በወል፣ ከፍተኛ የሆነ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ከ1972 ዓ.ም...Read more

ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ- የዘመናዊት ኢትዮጵያ አስተዳደር ቋሚ መሠረት ጣይ ፡- ዝክረ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ከልደት አስከ ሕልፈተ ሕይዎት።

Tuesday, March 29, 2016

ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ ለኢትዮጵያ ክብር፣ ነፃነት፣ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ማንነት ሲሉ፣ እጃቸውን ለእንግሊዝ ጦር መሪ ጄኔራል ናፒየር ከሚሰጡ ሞትን በመምረጥ ሽጉጣቸውን ጠጥተው ለኢትዮጵያዊነት ዳብሮ መቀጠል የተሰው ሰማዕት ንጉሠ ነገሥት መሆናቸው ዓለም ያወቀውና ያደነቀው አንጸባራቂ የታሪካችን አንዱ አካል ነው። ቴዎድሮስ ከእርሳቸው የነበሩት ንጉሦች መሠረታቸውን ይፋት፣ ሐረርና አዳል ባደረጉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ጋር ባደረጉት ተከታታይ ጦርነቶች፣ ተያይዞም...Read more

በሌሎች ተክዶ ራሱንም የካደው ትውልድ

የዘመናዊ  ትምህርት  ወይም  “ቀለም  ቀመስ”  የሆነው  የዐማራው  ትውልድ  በሌሎች  ነገዶች/ጎሣዎች  ቀለም  ቀመስ ትውልድ  ተክዷል።  በሌሎች  መካዱን  ያልተረዳውና  ሊረዳም  ያልፈለገው  ቀለም  ቀመሱ  የዐማራ  ትውልድ፣  የራሱን  ማንነት ክዶ  የገዛ  ትውልዱን  ከጥፋት  ለመከላከል  የሚያስችለውን  አቅሙን  ላለመጠቀም  የተለያዩ  ምክንያቶችን  በመደርደር  ራሱንና ወገኖቹን ለጥፋት አጋልጦ፣ “የራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለች” ዓይነት ሆኖ ይታያል።...Read more

Monday, November 18, 2013

Moresh Program

ኢትዮጵያ ረጅም የአገርነትና ተከታታይነት ያለው የመንግሥት ታሪክ ካላቸው ጥቂት አገሮች አንዷ ናት፡፡ የረጅም ዘመን አገርነቷና የተከታታይ በሀወርታዊ መንግሥት ባለቤት መሆኗ፣ በጥንታዊ ሥልጣኔ የቴክኖሎጂ ቅሬቶቿና በራሷ የጽሁፍ ቋንቋ የተገለጸ ነው፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙት የአክሱም ሀውልት፣ የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት፣ የጎንደር ቤተመንግሥቶችና ልዩ ልዩ ጥንታዊ መገልገያ መሣሪያዎች፣ የረጅም ዘመን ታሪኳ ቋሚ ነቃሾች ናቸው፡፡ በቅርቡ በምሥራቅ ኢትዮጵያ...Read more

Ato Tekle Yeshaw's Response to Dr. Lapiso

Ato Tekle reply to Dr. Lapiso part 1

እውነቱን ልነገርህ ስማኝ ፕሮፊሰር፣
ሰው ሞተ አይባልም ደግ ሰርቶ ቢቀበር፣
ብትችልማ ኑሮ አስመስሎ ማደር፣
አንተም እንደ ሰዎች መኖር ትችል ነበር፣

Pages

Subscribe to RSS - Amharic