የአገር ኩራት አስራት

ከፍያለው ጌቱ፣ ማክሰኞ ግንቦት ፲፰ ቀን ፪ሺህ፯ ዓም

እውነቱን ልነገርህ ስማኝ ፕሮፊሰር፣
ሰው ሞተ አይባልም ደግ ሰርቶ ቢቀበር፣
ብትችልማ ኑሮ አስመስሎ ማደር፣
አንተም እንደ ሰዎች መኖር ትችል ነበር፣
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አሁንም አልሞትህም እውነቱን ልንገርህ፣
ተተኪ ሰው አለ ከፍ  የሚል ከስርህ፣
በሰጠህን ማሳ ፍሬ ሚዘራልህ፣
አሁንም አልሞትህም እውነቱን ልንገርህ ፣
እናሸገራለን ሰፊ ነው ድልድይህ፣
አንተ ለኛ ስትል ብታልፍም ህይወትህ፣
ትናንት ተገናኘን ሊከበር ልደትህ፣
ደግመን ልንዘክርህ፣
ስምህን አውስተን ለትውልድ ልንሰጥህ፣
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የኢትዮጵያ የአገር ኩራት አስራት፣
የወገን አለኝታ መብራት የምትሰጥ ፋካት፣
አሰረህ ትተሓል የማይበጠስ ሰንስለት፣
አስቀምጠሓል የማይዝግ ብረት፣
ዋ ዋ አስራት ማለት ‘ያ’ ነው፡
ደግነት ብቻ ክፋት በውስጡ የለለበት ፣
የህዝብ አይን ነው አስራት ፣
የህዝብ የአማራ የወገን ኩራት፣
በነዛ በትናንሾቹ በጠላቶች ሰፈር፣
ከበሮ ሲመታ ሲጎሰም ነጋሪት ፣
እንደ ናዝሪት ጌታ ሲሰቅሉህ በሌሊት ፣
ልጆችህ አንድ ሁነው አንተ ባትነሳ ፡
ታሪክህን አነሱት ፣ዳግም አወገሱት ፣
ብርቀየ ስራሕን ደጋግመው አወሱት፣
ጠላቶችህ መጠው ስራህን ቢገፉት፣
ሞክረው ሊልጡት ዳግመኛ ቢለፉት፣
አፍሮ ተመለሰ ተሽክሞ ውርዴት፣
ማይችለውን ጭኖ ባነሰ ማንነት ፣
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከአባቶችህ የወረስህው፣
አስራት ታሪክህ ህያው ነው፣
ለዘላለም የማንረሰው፣
አፈር ምሰን የማንቀበረው፣
ደምህን ፈጅተህ ህይወትህን የገበርህው፣
ለዚህ የዋህ ህዝብ ብለህ ነው፣
አስራት ታሪክህ ህያው ነው፣
ዘላለም የማይጠፋን የማንረሰው፣
አስራት ልጆችህ ቃል ገብተናል፣
ውለታሕን ላንረሰው ፣
አስራት ታሪክህ እጹብ ድንቅ ነው፣
ከዘርዓያቆብ፣ከልብነድንግል፣
ከምኒልክ ፣ከቴዎድሮስ የወረስህው ፣
አስራት ታሪክህ ህያው ፣ህያው ነው፣
ገደብ ጣራ የለለው ህዝብ የማይሽረው፣
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የብስራት ልጅ አስራት ፣
የጨቋኞችን ቀንበር አልፈህ፣
ከአቅም በላይ ግፍ ተጭነህ፣
በጭላጭል ዘልቀህ ወጠህ ፣
ለአማራ ሰርተሓል ወያኔን እረስተህ፣
በአንድ አስተሳስረህ፣
ስር መሰረት ሁነህ፣
በሾህ አለንጋ እየተገረፍህ ፣
በጠባብ እስር ቤት ታስረህ፣
እንደ ስቃይ ሳታየው በደስታ አጣጥመህ፣
ለህዝብህ ልትሰጥ ፍትህ ፣
ተናግረህ በአንደበትህ ወገነህን ወደህ፣
የሰጠህን አደራ ይቀጥላል በራዕይህ፣
እንድታየን በመንፈስህ፣
አስራት ዘላለም ኗሪ ነህ፣
ጊዚያዊ ጥቅም ያልደለለህ፣
በውስጣችን የሰረጽህ፣
አስራት ማለት አንተ ነህ፣
ለአገር ፣ለወገን ለህዝብ የቆምህ፣
ጎዳናችን ያሳየህ ፍሬ ያፈራህ ፣
አንዱአለምን፣ ይልቃልን፣ እስክንድርን፣ አቢዮትን የወለድህ፣
አስራት ማለት አንተ ነህ ?
ያልሞትህ በህይወት ያለህ።